top of page
የወንድሞች ሕብረት August 27

በአካል ወደቤተክርስቲያን መጥተን እግዚአብሔርን በአንድ ላይ እንድናመልክ ስለረዳን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን! 

ካለው የኮሮና ችግር ምክንያትና በኮቪድ-19 መመሪያ መሰረት በየእሁዱ የተወሰነ ቁጥር ብቻ እናስተናግዳለን፡፡

መመሪያውን አንብበው በመመዝገብ አብረን ጌታን እናምልክ።

መመሪያ /Wavier

በአካል ተገናኝተን ስናመልክ ልናደርጋቸው የሚገቡ ጥንቃቴዎች

ለጥንቃቴ ሲባል የሚሩን ስብሰባዎች ለጊዜው በተወሰን ቁጥር በቻ ይሆናል

1.   ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጣ

 • ከቤት ከመውጣታቸው በፊት ምዕመናን ሳልና ትኩሳት፣ የራስ ምታት፣ የጉሮሮ መከርከር፣ የማሽተት ወይም የመቅመስ ስሜት ማጣት፣ የመተንፈስ ችግር፣ የደረት ሕመም ስሜት ካላቸው በቤታቸው ይቆያሉ።

 • መስፈርቶችን አሟልተው ወደ ጉባኤ ለመምጣት የሚፈልጉ በየሳምንቱ በኢንተርኔት ላይ መመዝገብ አለባቸው። በኢንተርኔት ለመመዝገብ እገዛ የሚፈልጉ ቤተክርስቲያን በ 214-703-0100 በመደወል በተፈለገው መንገድ ለመመዝገብ ይችላሉ።

 • ስልክ በመደወል መመዝገብ ለምትፈልጉ የምዝገባ ቀናት ከማክሰኞ እስከ አርብ ከ9፡00 AM – 5፡00 PM እንዲሁም ቅዳሜ ከ9፡00 AM – 12፡ 00 PM ብቻ ይሆናል።

 • ለደህንነታቸው ሲባል ዕድሜያቸው ከ 65 ዓመት በላይ የሆነ፣ ማናቸውም ዓይነት የጤንነት ችግር ያለባቸው፣ ወጣቶች፣ ህጻናት ልጆች አገልግሎቱን በኢንተርኔት አማካኝነት ከቤታቸው ይከታተላሉ፡፡

 • በምዝገባ ቅድሚያ አግኝተው ከተፈቀደላቸው ውጭ ሌሎች ምእመናን በሙሉ ከቤት ሆነው ይከታተላሉ።

 • አስተናጋጆችም የተመዝጋቢዎችን ስም ዝርዝር በመያዝ ካጣሩ በኋላ ወደ አምልኮ አዳራሽ ያስገባሉ።

 • ከቤት ከመውጣታቸው በፊት እጆቻቸውን በሳሙና መታጠብ እና ማስክ፣ Sanitizer መያዝን ማረጋገጥ

 • ቤተክርስትያን ሲደረስ የአስተናጋጆችን መመሪያ በመከተል አንድ ክፍት ቦታ በመዝለል ፓርክ ማድረግ።

 • የፊት ማስክዎን እስከ መጨረሻው አያውልቁ፡፡ ከሌሎች በቂ ርቀት እንጠበቅ፡፡ የአስተናጋጆችን መመሪያ እንከተል፡፡ ወደ አዳራሹ በተመደበው መግቢያ በኩል ብቻ ይግቡ፡፡

2. ወደ አምልኮ አዳራሽ ሲገባ የሚደረጉ ጥንቃቄዎች

 • መግቢያ በር ላይ የታዳሚዎችን ሙቀት (temperature) በርቀት ይለካሉ። የሙቀት መጠናቸው ከ100°F በላይ ሆኖ የተገኙ ምእመናን ወደቤታቸው እንዲመለሱ ይጠየቃሉ።

 • በቤተክርስቲያን በተዘጋጀው Hand Sanitizer ተጠቅመው ራሳቸውን ማጽዳት ይጠበቅብናል።

 • ርቀት በመጠበቅ በአስተናጋጆች መሪነት ምልክት በተደረገባቸው መቀመጫዎች ላይ ብቻ መቀመጥ።

 • ቤተሰብ ጎን-ለጎን ለመቀመጥ ተመዝግበው ቢመጡ አንድ አከባቢ ላይ ሊቀመጡ ይችላሉ።

 • በአዳራሽ ውስጥ ሳል ወይም ማስነጠስ ቢያጋጥም ማስኩን ሳያወልቁ ፊትን በንጹህ ወረቀት ወይም በክንድ በመሸፈን ማስነጠስ። የተጠቀምንባቸውንም ወረቀቶች (tissue ) ይዞ መውጣትና መጣል።

 • አባላት በተቻለ መጠን አስራቶቻቸውንና ሌሎች ስጦታቸውን online እንዲሰጡ ይበረታታሉ፡፡

 • ሆኖም ቼክ በመጻፍ ቤተክርስቲያን ተገኝተው ለሚሰጡ ስጦታቸውን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የመሰብሰቢያ እቃዎችን ውስጥ ያኖራሉ።

 • በመጸዳጃ ቤት ርቀትን ጠብቆ በአንድ ጊዜ የተወሰነ ሰው ብቻ እንዲገለገል አድርጎ መስተናገድ። 3. እርስ በርስ መተያየትና ሰላምታ መለዋወጥ

 • ከሌሎች አማኞች ጋር 6 ft. በመጠበቅና ማስክ በማድረግ እጅን በማውለብለብ ወይም ጎንበስ በማለት ብቻ ሠላምታ ይለዋወጣሉ ። መጠጋጋትና በእጅ መጨባበጥ ፈጽሞ አይፈቀድም።

 • የቤተክርስትያን አገልግሎት ሲያልቅ መጨናነቅን ለመቀነስ የ6 ft ርቀትን በጠበቀ ሁኔታ አስተናጋጆች እየመሩ ለመውጫ በተዘጋጁ በሮች ብቻ ምእመናን ይወጣሉ።

Wavier

COMMUNICABLE DISEASE

RELEASE OF LIABILITY AND ASSUMPTION OF RISK AGREEMENT

 

In consideration of being allowed to participate in any way in the program, related events and activities, I the undersigned, acknowledge, appreciate, and agree that:

 

I am aware there are risks to me of exposure directly or indirectly arising out of, contributed to, by, or resulting from an outbreak of any and all communicable diseases, including but not limited to, the virus “severe acute respiratory syndrome coronavirus 2 (SARS‐CoV‐2)”, which is responsible for Coronavirus Disease (COVID‐19) and/or any mutation or variation thereof.

 

I, for myself and on behalf of my heirs, assigns, personal representatives and next of kin, HEREBY RELEASE, INDEMNIFY, AND HOLD HARMLESS EEBC from any and all claims, demands, losses, and liability arising out of or related to any ILLNESS, INJURY, DISABILITY OR DEATH I may suffer, WHETHER ARISING FROM THE NEGLIGENCE OF THE RELEASEES OR OTHERWISE, to the fullest extent permitted by law.

 

I HAVE READ THIS RELEASE OF LIABILITY AND ASSUMPTION OF RISK AGREEMENT, FULLY UNDERSTAND ITS TERMS, UNDERSTAND THAT I HAVE GIVEN UP SUBSTANTIAL RIGHTS BY SIGNING IT, AND SIGN IT FREELY AND VOLUNTARILY WITHOUT ANY INDUCEMENT.

 

 

FOR PARENTS/GUARDIANS OF PARTICIPANT OF MINOR AGE (UNDER AGE 18 AT TIME OF REGISTRATION)

 

This is to certify that I, as parent/guardian with legal responsibility for this participant, do consent and agree to his/her release as provided above of all the Releasees, and, for myself, my heirs, assigns, and next of kin, I release and agree to indemnify and hold harmless the Releasees from any and all liability incidents to my minor child’s involvement or participation in these programs as provided above, EVEN IF ARISING FROM THE NEGLIGENCE OF THE RELEASEES, to the fullest extent permitted by law.

bottom of page